1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከድርቅ ወደ ለምለም ዉይይት

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ግንቦት 15 2008

ኢትዮጵያን በመታዉ ድርቅ ለችግር የተጋለጠዉን ሕዝብ ለመርዳት መንግስትን ጨምሮ የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ርዳታ ለማድርስ እየተሯሯጡ ይገኛሉ። ርዳታ ከመስጠት ጎን ለጎን በተለያዩ ቦታዎች መድረኮች ተከፍቶ ድርቁን መቋቋም በሚቻልበት ሥልት ላይ ዉይይት እየተካሔደ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/1ItCW
Deutschland Zentrale der Deutschen Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit
ምስል picture-alliance/dpa/F. Rumpenhorst

[No title]

ባሳለፍነዉ ሮብ ቦን ከተማ የጀርመን ልማት ትብብር፣ /GIZ/ ያዘጋጀዉ ዉይይትም በዚሁ ላይ ያተኮረ ነበር። ዉይይቱ <<Wenn die Wüste wieder grün wird – Dürre erfolgreich bekämpfen>> ማለት <በረሐዉን ዳግም ለምለም ማድረግ፤- ድርቅን በተሳካ ሁኔታ መታገል> የሚል ርዕስ ተሰጥቶ ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር መጨመሩ፣ የአፈር መንሸርሸር እና የግጦሽ ቦታዎች መጥበብ ድርቁ የሚያደርሰዉን ችግር ካባባሱት ምክንያቶች አንዱ ነዉ የሚሉት የመድረኩ ተሳታፍ እና በኢትዮጲያ የGIZ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዮሃንስ ሾነቤርጌር ናቸዉ። እንደእሳቸዉ ገለጻ በዓመት በኢትዮጵያ 1,5 ቢሊዮን ቶን አፈር በመሬት መንሸርሸር ምክንያት ይታጠባል። ይሕ በግብርናዉ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለዉ ስራ አስኪያጅ እንድህ ያብራራሉ፣ <<ሌላኛዉ ለኢትዮጵያ መንግስት ከባድ ችግር የሚሆነዉ አሁን እየተገነቡ ያሉት ግድቦች ናቸዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ነፁሕ የመብራት ሃይል ለማቅረብ እና የተሻለ ህይወት ለመምራት ብሎ ብዙ ቦታዎች ላይ ግድቦችን እየገነባ ይገኛል። ይህ ግድብ ሙሉ በሙሉ ከተናቀቀ ከግማሽ በላይ የመሬት መንሸርር እንደሚቀንስ ይጠበቃል። ይሄን ችግር መንግስት ያዉቃል እናም በብሄራዊ ደረጃ ቋሚ የመሬት አስተዳደር የሚባልዉን ፕሮግራም ተጠቅሞ ከ600 ችግሩ ካለበት ቦታዎች 177ቱ ላይ የመሬት መንሸርሸርን የሚያቆም እናም መልሶ እንዲለም ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።>>

Dr. Johannes Schoeneberger
በኢትዮጲያ የGIZ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዮሃንስ ሾነቤርጌርምስል DW/K. Jäger


የኢትዮጵያ መንግስት <<የልማት አጋር ነን» የሚሉት ዶክተር ዮሃንስ ሾነቤርጌር የአፈር መንሸርሸርን ለመጠበቅ እና መሬቱን መልሶ ለማልማት ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር እየሰራን ነዉ ይላሉ። ዜሮ የመሬት መንሸርሸር ለማሳካት በፖለቲካ ደረጃ መንግስትን ማሳመን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ሌላኛዉ ተሳታፊ የተባበሩት መንግስታት በረሃ የማቆም ኮንቬንሼን ሰራተኛ ዶክተር አሌክስአንዴር ኤርሌቫይን ይናገራሉ።በግብርና ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ የአፈር መንሸርሽር ማቆም ዋናዉ አለማዉ መሆን እንዳለበትም ይጠቅሳሉ። የመሬት መሸርሸርን በተመለከተ በብሄራዊ ደረጃ መደረግ ያለበትን ዶክተር አሌክስአንዴር እንድህ ይላሉ፣ <<ብሄራዊ የድርጊት መረሐ-ግብር የሚባለዉ የኮንቬንሸኑ ትልቅ መሳርያ ነዉ።የኮንቬንሸኑ አባል የሆኑት ይሄን ዕቅድ ስራ ላይ ለማዋል እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚያም አገሮች የሚያመጡት መልስ የተለያየ ሲሆን፤ የመሬት መንሸርሽር ላይ መረጃ ይለዋወጣሉ። አዲስ ነገር የሆነዉ መሬት የተፈጥሮ ይዞታዉን የሚቀይረዉን የመሬት መንሸራሸርን ለመቀንስ በብሄራዊ ደረጃ በተለያዩ መንገዶች መጠቀም መጀመራቸዉ ነዉ።»

Äthiopien Afar angestautes Wasser
የGIZ ፕሮጄክት በአፋር ክልልምስል DW/G. Tedla


ዶክተር ዮሃንስ ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር ሆነዉ እስካሁን ስላለሙት መሬት እንድህ ይናገራሉ፣ <<እኔ ለማለት የምፈልገዉ የኢትዮጲያ መንግስት በመሬት ላይ የያዘዉን ፕሮግራም በገንዘብ እንረዳዋለን፣ ለምሳሌ በቡና ቴክንክ ላይ ያለዉን። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሆነን ተሸርሸረዉ የነበረዉን 390,000 ሄክታር መሬት መልሰን አልምተናል። ሌላኛዉ ደግሞ የመሬቱ ዉጤታማ መሆንን በተመለከተ በፊት በረሃ የነበሩ ተመልሰዉ ለምለም ሲሆን የእትዮጵያ ገበሬዎች እንደሚሉን ከአምስት አመት በዋላ መሬቱ የሚሰጠዉ ምርት ከ35 እስከ 80 በመቶ መጨመሩን ነዉ። ይህም ትልቅ ነገር ነዉ።>>

Äthiopien Dürre in Gelcha
ድርቅ ያጠቃት ከብት በጌልቻምስል Reuters/T. Negeri


በዉይይቱ ወቅት በአገርቱ ዉስጥ ያለዉት የመሬት ባለቤትነት መብትን እና የመሬት ቅርምት ጋር ተያይዞ የሚመጡት ችግሮችም ተነስተዋል። የእትዮጵያ መንንግት የመሬት መቀረማት የሚለዉን አስተሳሰብ ባይጠቀምም የዉጭ አገር ባለሐብቶች በግብርናዉ መስክ ሥራ ላይ ሲሰማሩ በየአካባቢዉ ከሚኖረዉ ማሕበረሰብ ጋር ግጭት መፈጠሩን ዶክተር ዮሃንስ ሾነቤርጌር ጠቅሶዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ