1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከግሪክ የተላኩ የፓኬት ቦምቦችና ያስከተሉት ስጋት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2003

ለጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የተላከ አንድ ፈንጂ የያዘ ፓኬት ትናንት በመራሄ መንግስቱ ጽህፈት ቤት ከደረሰ በኋላ ማምከን መቻሉ ታውቋል።

https://p.dw.com/p/PxEW
ምስል DAPD

የጀርመን ሀገር አስተዳደር ሚንስትር ቶማስ ደ ሜዝየር እንደገለጹት፡ ፓኬቱ የመጣው ከግሪክ ነው። ለኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ የተላከ ፈንጂ የያዘ አንድ ሌላ ፓኬት ደግሞ የኢጣልያ ፈንጂ አምካኞች እጅ ቢቀጣጠልም፡ ጉዳት አለማድረሱ ተሰምቶዋል። ለፓኬቶቹ ቦምቦች የግሪክ የግራ አክራሪዎች ተጠያቂ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተጠርጥሮዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ