1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጫማ ጠራጊ እስከ ዮንቨርስቲ መምህርነት

ዓርብ፣ ጥቅምት 19 2008

ትምህርት ማግኘት የሰብዓዊ መብት ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ ለሚኖሩ ወጣቶች ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ብዙ ፈተናዎች አሉት። ስለሆነም ትምህርታቸውን አጠናቀው የስራውን ዓለም መቀላቀል የሚችሉት ጥቂቶች ናቸው።ክንዴ ባንቲ ፤ ጎጃም ውስጥ አዊዞን አካባቢ ነው ተወልደው ያደጉት። ዛሬ በጎንደር ዮንቨርስቲ በመምህርነት ያገለግላሉ።

https://p.dw.com/p/1Gwez
Schüler in einem Dorf in Äthiopien
ምስል picture-alliance/ dpa

ከጫማ ጠራጊ እስከ ዮንቨርስቲ መምህርነት

እዚህ ለመድረስ ያሳለፉትን ጊዜ ግን መለስ ብለው ሲያስታውሱ ብዙ ችግሮችን እንዴት እንዳሳለፉ ነው።መምህር ክንዴ በአርዓያነት የሚጠቅሷቸው አቶ ጌትነት አምሀ ከአዲስ አበባ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የፍቼ ከተማ ነው ተወልደው ያደጉት። ትምህርታቸውን አጠናቀው በወቅቱ ጎጃም ውስጥ ለስራ ተመድበው በሄዱበት ጊዜ ነው ከዛሬው መምህር ፤ ከያኔው ወጣት ክንዴ ጋር የተገናኙት። ጊዜው ብዙ ሩቅ ቢመስልም መምህር ክንዴ 30ቹ አጋማሽ ላይ የሚገኙ ጎልማሳ ናቸው። የሳቸው ታናሽ ወንድም እና እህት ትምህርት ቤቱ ሩቅ በመሆኑ እና እንደ ወንድማቸው አስጠግቶ የሚያኖራቸው ባለመኖሩ የመማር እድል አልገጠማቸውም። የመምህር ክንዴም መማር ጠቀሜታው በወላጆቻቸው ዘንድ እውቅና እስኪያገኝ ጊዜ ፈጅቷል። በአዊዞን አካባቢ አሁን ያለው የመማር ማስተማር ሁኔታ እና የአካባቢው ነዋሪ ለትምህርት ያለው ግንዛቤ ተቀይሯል ይላሉ መምህር ክንዴ።

ገጠር ውስጥ ትምህርት ለመማር ብዙ ፈተና ያሳለፉ እና በመጨረሻም የከፍተኛ ተቋም መምህር እስከመሆን የበቁት ክንዴ ባንቲ እና አርአያዬ የሚሏቸው ጌትነት አመሃ ፤ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ ስለነበረው የትምህርት ሁኔታ የገለፁልንን በድምፅ ዘገባ ያገኛሉ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ