1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፍተኛ የታክስ ጭማሪ እና ሮሮ

ረቡዕ፣ ሰኔ 28 2009

በኢትዮጵያ በንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች ከፍተኛ የሆነ ዓመታዊ የታክስ ክፍያ እንድንፈጽም ተመድቦብናል ሲሉ በማማረር ላይ ናቸው። አስተያየት ሰጪዎች የታክስ ክፍያ ተመኑ ከአቅም በላይ በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም ብለዋል። ከወራት በፊት ወደመጣሁበት ዓረብ ሀገር እመለሳለሁ ያሉም አሉ።

https://p.dw.com/p/2fyn5
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

Beri. AA, (Public complaints on Tax collection) - MP3-Stereo

ከአዲስ አበባ በደረሰን ዘገባ መሠረት ግብር ከፋዮች ከአቅም በላይ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ክፍያ ተጥሎበቸው እያማረሩ ነው። ከዚህ ቀደም እስካሁን ድረስ በዓመት 3000 ብር ነበር የምከፍለው። አሁን ደግሞ በቀን ገቢ 1800 ብር ዓመታዊ አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ አድርገውት ፣አይደለም መክፈል ምንም ማድረግ አንችልም» ይላሉ አንድ ነጋዴ። ከዓረብ ሀገር ከመጣች ገና አራት ወር የሆናት ደግሞ የግብሩ መጠን ከአቅሟ በላይ እንደሆነ በመግለጥ ወደ ዓረብ ሀገር ዳግም ለመሰደድ መቁረጧን እንባ እየተናነቃት ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግራለች። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ