1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቀዉ የአየር ንብረት ለዉጥ

ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2008

የአየር ንብረት ለዉጥን ለመግታትም ሆነ ከለዉጧ ጋር ተላምዶ ለመኖር ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቅ የዘርፉ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ በጥናት አስደግፈዉ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/1HG1I
Australien plant Reduzierung von CO2 Emissionen
ምስል Getty Images/AFP/P. Crock

ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቀዉ የአየር ንብረት ለዉጥ

ወደከባቢ አየር ከፍተኛ የበካይ ጋዝ መጠን የሚለቁት ሃገራት የግል ብልፅግና እና የልማት እድገታቸዉ እንዳይደናቀፍ በመስጋት ሊወስዱት የሚገባዉ ርምጃ ላይ መወሰን የቻሉ አይመስልም። በካይ ጋዙ ባስከተለዉ የአየር ንብረት ለዉጥ መዘዝ የተጋለጡ ሃገራት ከበለፀጉት የኢንዱስትሪ ቱጃሮች የሚጠብቁት የገንዘብ ድጋፍ በፓሪሱ የአየር ንብረት ተመልካች ጉባኤም ዋነኛ አነጋጋሪ ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። አንድ ሀገር ወደከባቢ አየር በሚለቀዉ የበካይ ጋዝ መጠን ምን ያህል ገንዘብ ለዚህ መክፈል ይኖርበታል የሚለዉም አከራካሪ ነዉ። ኤኮኖሚ ባለሙያዎች ግን መፍትሄ ያሉትን በጋራ የበጎ አድራጎት የልማት ድርጅት ቢቋቋም እንደሚበጅ እየመከሩ ነዉ። የዕለቱ ከኤኮኖሚዉ ዓለም ይህን ይመለከታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ