1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ታሪክ

የታንዛኒያ የነጻነት ተጋድሎ ፈር ቀዳጅ

ሐሙስ፣ መጋቢት 27 2010

ኪንጄኬቲሌ ንጓሌ በአፍሪቃ ታሪክ አወዛጋቢ ሥፍራ አላቸው። በ20ኛው ክፍለ-ዘመን መባቻ አኹን ታንዛኒያ ብለን የምንጠራት ሀገር ዜጎች የጀርመን ቅኝ ገዢዎችን ተቃውመው እንዲታገሉ አበረታትተዋል። ተከታዮቻቸው ጥይት እንዳይመታቸው የሚጋርድ የተቀደሰ ውኃ አለኝ ሲሉ ቃል በመግባታቸውም ይታወቃሉ። አንዳንዶች ኪንጄኬቲሌን ለሕዝባቸው ተስፋ እና ብርታትን ያሰነቁ ጀግና አድርገው ይመለከቷቸዋል። ሌሎች ደግሞ ሰውዬው ሕዝባቸውን ወደ ሞት የነዱ አታላይ ነበሩ ይሏቸዋል።#ARAMH

https://p.dw.com/p/2vXN1