1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«መዝናኛ» መፅሔት

ዓርብ፣ ጥር 11 2010

የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዳችን በካናዳ «መዝናኛ» የተሰኘ መፅሔት መስራች እና ዋና አዘጋጅ ነው። ዳንኤል ገብረማሪያም ይባላል።

https://p.dw.com/p/2r8yC
Äthiopien Meznagna Magazin
ምስል DW/ D. Gebremariam

ካናዳ የሚታተመው «መዝናኛ» መፅሔት

«መዝናኛ» ካናዳ ውስጥ በየሁለት ወሩ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለአንባቢያን የሚቀርብ መፅሔት ነው። የመፅሔቱ መስራች እና ዋና አዘጋጅ ዳንኤል ገብረማሪያም እንደሚለው መፅሔቱ ትኩረቱን ያደረገው ወጣቶችን በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው። «ወጣቱ ባህሉን እና ማንነቱን እንዲያከብር ነው እኛ የምንፈልገው ይላል። ዳንኤል ይህንን መፅሔት እንዲጀምር የገፋፋው ሔኖክ አበጀ የተባለው ጓደኛው እንደሆነ ይናገራል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ አሌክሳንደር ሰማሁ ከተባለ ጓደኛው ጋር መፅሐፉን በጋራ ያዘጋጃል። መፅሐፋ መታተም ከጀመረ ሁለት ዓመት አስቆጥሯል። ዳንኤልም ሙሉ ትኩረቱን አሁን ወደ መፅሔቱ አድርጓል።
ዳንኤል «ተፅዕኖ ፈጣሪ» ናቸው የሚላቸውን እውቅ ኢትዮጵያውያን እንግዶቹ አድርጎል። ካናዳ ውስጥ በራሱ ቋንቋ የራሱን መፅሔት ማሳተም በመቻሉም ደስተኛ ነው። በመፅሄቱ የተለያዩ ርዕሶችን ለመዳሰስ ይሞክራል።
መፅሔቱ እስካሁን በሰሜን አሜሪካ ሲሆን ለገበያ የቀረበው ወደፊት ደግሞ ወደሌሎች አህጉሮች የማከፋፈል እቅድ እንዳለው ዳንኤል ይናገራል።  ኢትዮጵያ ጃፓን እና አውስትራሊያ ሀገራት በአሁኑ ሰዓት ትኩረት አግኝተዋል።  
«መዝናኛ» መፅሔት ታትሞ ብቻ ሳይሆን በዲጂታል መልክም ኢንተርኔት ላይ ይገኛል። አዘጋጁ ዳንኤል በካናዳ ሲኖር 10 ዓመታት ተቆጠሩ ፤ ኢትዮጵያ እያለም ከመገናኛ ብዙኃኑ ዓለም ብዙ አልራቀም ነበር።   
በካናዳ «መዝናኛ» የተሰኘ መፅሔት መስራች እና ዋና አዘጋጅ ዳንኤል ገብረማሪያም ከዶይቸ ቬለ ጋር ያደረገውን ቆይታ መስማት ከፈለጉ  የድምፅ መልዕክቱን ይጫኑ።

Äthiopien Meznagna Magazin
የ «መዝናኛ» መፅሔት መስራች እና ዋና አዘጋጅ ዳንኤል ገብረማሪያምምስል DW/ D. Gebremariam


 ልደት አበበ
አርያም ተክሌ