1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያና የ«ሣር ምድሩ ሲሊከን»

ረቡዕ፣ ጥቅምት 28 2005

በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም በአሁኑ ጊዜ የሥነ-ቴክኒክ-አብዮት በመካሄድ ላይ ነው። የመረጃ ሥነ ቴክኒክን በተመለከተ ፣ አፍሪቃ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከቀሪው ዓለም ጋር መተሣሰር እንዳልቻለ ነበረ የሚታወቀው። በአሁኑ ቅጽበት ግን 13 ከመቶ

https://p.dw.com/p/16fAn
ምስል picture alliance/dpa

የአፍሪቃ ህዝብ ከዓለም አቀፍ የመረጃ መረብ ጋር መተሣሰሩ ነው የሚነገረው። ይህ ፣ የሆነው ሆኖ ከሌሎች ክፍላተ ዓለም ዜጎች የመረጃ የአጠቃቀም መጠን ጋር ሲነጻጸር ፣ በጣም ጥቂት ነው። በአውሮፓ 74 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በዘመናዊው ሥነ ቴክኒክ ተጠቃሚ ነው። ይሁንና በአፍሪቃ፣ በዚህ ዘመናዊ የመረጃ ሥነ ቴክኒክ የመጠቀሙ ጉጉትና እርምጃ መስተፋጥናዊ እንቅሥቃሴ እየታየበት ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት3 ከመቶ ብቻ የነበረው አሁን 13 ከመቶ ደርሷል።

Handy wird zum Einkaufsberater
ምስል picture-alliance/dpa

በግልጽ እንደታየው፣ ለመረጃው ሥነ ቴክኒክ መሥፋፋትም ሆነ መጨመር መሠረት የሆነው፣ በባህር ወለል የተዘረጋው፣ አፍሪቃን ከአውሮፓና እስያ ጋር የሚያገናኘው የተንቀሳቃሽ ሥዕልና ድምፅ እንዲሁም ጽሁፍ ማሠራጫው ልዩ ሽቦ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የመረጃ ሥነ ቴክኒክ እጅግ ከሚስፋፋባቸው አገሮች አንዷ፣ የኢትዮጵያ ጎረቤት ፣ ኬንያ ናት።

በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም በአሁኑ ጊዜ የሥነ-ቴክኒክ-አብዮት በመካሄድ ላይ ነው። የመረጃ ሥነ ቴክኒክን በተመለከተ ፣ አፍሪቃ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከቀሪው ዓለም ጋር መተሣሰር እንዳልቻለ ነበረ የሚታወቀው። በአሁኑ ቅጽበት ግን 13 ከመቶ የአፍሪቃ ህዝብ ከዓለም አቀፍ የመረጃ መረብ ጋር መተሣሰሩ ነው የሚነገረው። ይህ ፣ የሆነው ሆኖ ከሌሎች ክፍላተ ዓለም ዜጎች የመረጃ የአጠቃቀም መጠን ጋር ሲነጻጸር ፣ በጣም ጥቂት ነው። በአውሮፓ 74 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በዘመናዊው ሥነ ቴክኒክ ተጠቃሚ ነው። ይሁንና በአፍሪቃ፣ በዚህ ዘመናዊ የመረጃ ሥነ ቴክኒክ የመጠቀሙ ጉጉትና እርምጃ መስተፋጥናዊ እንቅሥቃሴ እየታየበት ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት3 ከመቶ ብቻ የነበረው አሁን 13 ከመቶ ደርሷል።

በግልጽ እንደታየው፣ ለመረጃው ሥነ ቴክኒክ መሥፋፋትም ሆነ መጨመር መሠረት የሆነው፣ በባህር ወለል የተዘረጋው፣ አፍሪቃን ከአውሮፓና እስያ ጋር የሚያገናኘው የተንቀሳቃሽ ሥዕልና ድምፅ እንዲሁም ጽሁፍ ማሠራጫው ልዩ ሽቦ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የመረጃ ሥነ ቴክኒክ እጅግ ከሚስፋፋባቸው አገሮች አንዷ፣ የኢትዮጵያ ጎረቤት ፣ ኬንያ ናት።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ