1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ኢትዮጵያ በኬንያ በለሙ ወደብ እንድተገነባ መሬት ልሰጣት ነዉ

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ግንቦት 1 2010

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከትላንት ወድያ በኬንያ ባደረጉት ጉብኝት ከአቻቻዉ ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጋር በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸዉን ጉቭንቱን አስመልክቶ የወጣዉ መግለጫ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/2xSdT
Karte Kenia Englisch

Ethiopia to build logistic faciltiy in Kenya - MP3-Stereo

ኬንያ በለሙ ወደብ አከባቢ ኢትዮጵያ ስራን ማቀላጠፍ የሚያስችላት ግንባታ የምታካሂድበት መሬት እንደምታቀርብ፤ ኢትዮጵያም ግንባታውን ለማካሄድ ቆርጣ መነሳቷን ማሳወቋ በመግለጫዉ ተጠቅሷል።

ስምምነቱ የስራ እድል እንደሚፈጥር፤ የዉጭ ገበያን እንደሚያቀላጥፍ፤ ኬንያም ሁለተኛ ወደቧን ለመስራት እንደሚረዳት እና ኢትዮጵያ አማራጭ የወደብ በር እንዲኖራት እንደሚያደርግ የኬንያ የዉጭ ጉዳዮችና የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር የኮሙኒኬሼን ሃላፊ ኤድዊን ሊሞ ለዶይቼ ቬሌ በላኩት እሜል ገልጸዋልዋል።

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም ጋር ለመገበያየት በዋነኛነት የምትጠቀመዉ የጅቡቲን ወደብ ነው። ሆኖም የተለያዩ አማራጮች ቢኖሯት የአገሪቱን እድገት እንደሚያቀላጥፍ የሎጂስቲክስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥለሁን ሙሉጌታ ይናገራሉ።

በጭነት ማስተላለፍ ስራ ላይ የተሰማራ የድስፓችድ እንቴርናሽናል ሎጅስትክ ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ አላዛር ጌታቸዉ ኢትዮጵያ በለሙ ላይ ሥራ ማቀላጠፍ የሚያስችላት ግንባታ ማካሄዷ ለሁለቱም አጋራት ጠቀሜታ እንዳለዉ ያስረዳሉ።

ሁለቱ አገራት ከኢሲኦሎ-ሞያሌ-ሃዋሳ-አድስ አባባ የሚያገናኝ መንገድ፤ በተመሳሳይም አዲስ አበባን ከናይሮቢ የሚያገናኝ  የባቡር መስመር ለማልማት መስማማታቸዉን መግለጫዉ ያመለክታል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ