1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ክትትል የሚሻዉ የሴቶች ጤና

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2001

በአገራችን ተስፋፍቶ የኖረዉ የሴትን ልጅ የመዋለጃ አካላት መቁረጥ ጊዜያዊም ሆነ ዘላቂ የጤና እክል ያስከትላል።

https://p.dw.com/p/Gr3s
....ጥንቃቄ ለሴቶች...
....ጥንቃቄ ለሴቶች...ምስል picture-alliance/ dpa

ሴቶች በዚህ አስከፊ ልማዳዊ ተግባር ሰበብ ለተለያዩ የማህፀን ህመምና የወሊድ ችግሮች ይዳረጋሉ። ከዚህም ሌላ በአገራችን ተከታታይ ምርመራ ባለማድረግ መዘዝ በቀላል ህክምና ሊድን የሚችለዉ የማህፀን ጫፍ ነቀርሳ የብዙዎችን ህይወት ከማጨለም አንስቶ እስከማሳለፍ ይደርሳል።