1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ መስተዳድ እርምጃ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 15 2012

ዶክተር ፋንታሁን እንዳሉት ከዚህ በፊት  12 ሰዎችን ያሳፍሩ የነበሩ የከተማ ታክሲዎች  8 ሰዎችን ብቻ እንዲጭኑ፣ እስካሁን 3 ሰዉ ይጭኑ የነበሩ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ወይም ባጃጆች ደግሞ 2 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መስተዳድሩ ደንግጓል

https://p.dw.com/p/3Zyg4
Dr. Fanta Mandefro
ምስል DW/A. Mekonnen

የኮሮና ተሕዋሲን ለመከላከል የአማራ ክልል ደንብ

             

የአማራ ክልላዊ መስተዳድር የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን መከላከል ያስችላል ያለውን እርመጃ ደንብ አወጣ።ነዋሪዎቹ ግን የመስተዳድሩ አንዳድ ደንቦች ዉጤት ማምጣታቸዉን ይጠራጠራሉ።የአማራ  ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ ትናንት ማምሻውን ለጋጠኞች በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት ስርጭቱን ለመከላከል በተለይ  በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ አዲስ አሰራር ደንግጓል፡፡ዶክተር ፋንታሁን እንዳሉት ከዚህ በፊት  12 ሰዎችን ያሳፍሩ የነበሩ የከተማ ታክሲዎች  8 ሰዎችን ብቻ እንዲጭኑ፣ እስካሁን 3 ሰዉ ይጭኑ የነበሩ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ወይም ባጃጆች ደግሞ 2 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መስተዳድሩ ደንግጓል።በክልሉ የሚገኙ መሸታ ቤቶች፤አዝማሪና ጭፈራ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እንዲዘጉ ተወስኗልም።

 ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ