1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሶቫ ከአንድ ዓመት በኃላ

ሐሙስ፣ የካቲት 12 2001

የቀድሞዋ ዩጎዛቭያ አንዷ ግዛት፣ ዩጎዝላቪያ ከተበታተነች በኃላ ደግሞ የሰርቢያ አንዷ ክፍለ ሀገር የነበረችው ኮሶቮ የአንድ ወገን ነፃነት ያወጀችበት አንደኛ ዓመት ከትናንት በስተያ ተከበሯል ።

https://p.dw.com/p/GxeQ
ምስል picture-alliance/dpa

አምና በይፋ ራሷን ከሰርቢያ ስትገነጠል ከምዕራቡ ዓለም ብዙ ተስፋ የተሰጣት ኮሶቮ ነፃነት ያወጀችበትን አንደኛ ዓመት ያከበረችው ከበርካታ ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮቿ ጋር ነው ። ብዙሀኑ አልባንያውያን ኮሶቮ አምና ስትገነጠል ደስታቸውን ወሰን አልነበረውም ። አሁን ግን በዓመቱ ሁኔታዎችን ወደ ኃላ መለስ ብለው ሲመለከቱ የህዝቡን ህይወት ለመቀየር ከፖለቲካዊ ንግግሮች በላይ መከናወን ያለባቸው ብዙ ተግባራት እንዳሉ መገንዘብ ጀምሯል ።