1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅቱን ያልጠበቀዉ ዝናብ በሐረሪ

ሐሙስ፣ ኅዳር 5 2006

በሐረሪ ክልል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ። የአካባቢዉ ገበሬዎችና ኗሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት በማሳ ላይ ያለ የስንዴና ገብስ ሰብል እየረገፈ፤ አንዳንዱ ሰብልም ማሳላ እያለ መልሶ በቅሏል።

https://p.dw.com/p/1AHe8
ምስል DW

ከዚህም ሌላ በዚሁ ዝናብ ምክንያት ከሃያ የሚበልጡ ቤቶች ፈራርሰዋል። የክልሉ የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ቢሮ በበኩሉ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ማስጠንቀቂያዉን አሰራጭቻለሁ፤ ይህንን ተጠቅሞም አርሶ አደሩ ምርቱን እየሰበሰበ ነዉ ይላል። መስሪያ ቤቱም አስፈላጊዉን ድጋፍም እያደረገ መሆኑን ይገልጻል። በሌላ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ አርሶ አደሮች ደግሞ ሰብሉ ከመጎዳቱ አስቀድመዉ በዘመቻ ለመሰብሰብ እየሞከሩ እንደሚገኙ ተነግሯል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ