1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወታደራዊው ጁንታና ውጥረት በጊኒ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2001

ትናንት እናንተ በስልጣን ላይ ቆያችሁ፤ ዛሬ ደግሞ ተራው የኛ ነው...ለጥበቦ አሁንም በድጋሚ እናመሰግንዎታለን ክቡር ፕሬዚዳንት...

https://p.dw.com/p/GNRi
ሟቹ ፕሬዚዳንት ላንሳና ኮንቴ
ሟቹ ፕሬዚዳንት ላንሳና ኮንቴምስል picture-alliance/ dpa
የጊኒ የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት የተሰጣቸው የሃያ አራት ሠአታት ቀነ ገደብ ሳይገባደድ ዛሬ ለወታደራዊው ጁንታ መግባታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ።ጊኒን ለሃያ አራት አመታት በአምባገነንነት ሲገዟት ቆይተው ባለፈው ሰኞ ያረፉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላንሳና ኮንቴ ዜና ረፍትን ተከትሎ ወታደራዊ ጁንታ የአመራሩን ቁንጮ መቆጣጠሩን ገልፆ እንደነበር ይታወቃል። የቀድሞ የመንግስት ባለ ስልጣናት ዛሬ ዋና ከተማዋ ኮናክሬ ተገኝተው የጁንታው መሪ ሻለቃ ሞሳ ዳዲስ ካማራን ፕሬዚዳንት ማለታቸውም ታውቓል።