ኤኮኖሚ
ወደ ማሳ የቀረቡት የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያዎች
ረቡዕ፣ ጥር 29 2011ማስታወቂያ
የይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመጪዎቹ ሁለት ወራት የመጀመሪያ ምርቶች ይፋ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሩ ወልዴ ለDW እንደ ተናገሩት የአቮካዶ እና የማር አቀነባባሪዎች የሚጠቀሙባቸው መጠለያዎች ተጠናቀዋል። በሥራው ለመሰማራት የፈለጉ ኩባንያዎችም ማሽኖችን ከቦታው አድርሰዋል።
አቶ ብሩ "ከሁለት ወር በኋላ የዘይት ምርት ይጀመራል ብለን እንጠብቃለን። ለዚህ ቅድመ-ዝግጅት ቀን ከለሊት እየሰራን እንገኛለን። ካምፓኒዎችም ማሽነሪዎች አምጥተው ግንባታው በሚካሔድበት ቦታ አስቀምጠዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ብሩ እንደሚሉት የማሰልጠኛ እና የገበያ ማዕከል ግንባታዎች ተካሒዷል። የፓርኩ የአስተዳደር ሕንጻ ግንባታም ተጠናቋል። የውሐ እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቶች ተሟልተውለታል። የመንገድ ግንባታው በመካሔድ ላይ ነው።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ