1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣቱና ቁጠባ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2005

ልብ በአርባ ዓመት ብር በሃያ ዓመት ይላሉ አበዉ ። ይህ በየትኛዉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚሠራ አባባል ነዉ ቢባል አያጣላም። በወጣትነት ጉልበቱ እያለ ተሯሩጦ ሠርቶ ጥሪት መቋጠር የተሳካለት ራሱን ለመቻል ሲሯሯጥ፤ በዚሁ እድሜ እንዲሁ ያገኘዉን ከእጅ ወደአፍ አይነት እያባከነ ዓላማዉን ለማሳካት የሚሳነዉ ቁጥሩ ቀላል አይደለም።

https://p.dw.com/p/17AuP
ምስል fotolia/HLPhoto

በምዕራቡ ዓለም በተለይ እዚህ ጀርመን ሀገር ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ገና ከለጋ እድሜያቸዉ አንስተዉ የገንዘብ አያያዝና አወጣጡን ለማያሰት ለማለማመድ ይጥራሉ። ሁሉም ግን ይሳካላቸዋል ማለት ይከብዳል።

ለመሆኑ ወጣቱ ምን ያህል ይቆጥባል? በሚል ካነጋገርናቸዉ መካከል ምንም እንኳን በአሁን ጊዜ ኑሮ የተወደደ ቢሆንም አንደኛዋ እንግዳችን በምታገኘው 8000 ብር የተጣራ ገቢ ሁለት እና ሶስት ቤተሰብ ማስተዳደር ይችላል ባይ ናት። እሷ ግን በወር ብቻዋን ታጠፋዋለች። ለምን መቆጠብ ይቸግራታል?

ምንም እንኳን ወለዱ ለቁጠባ የሚያበረታታ ባይሆንም፤ ጨርሶ የቁጠባ ባህል በህብረተሰቡ ዘንድ በደንብ አልተስፋፋም። በዚህ ረገድስ ወጣቱ ለወደፊቱ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ