1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

13 ዓመት የሆስፒታል አልጋ ቁራኛ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 26 2010

ኢትዮጵያዉያኑ የእግር ኳስ ግጥሚያ እና የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት እስካሁን ሐምሳ ሺሕ ሪያል አዋጥተዋል።ኢትዮጵያዉያኑ ላነሱት የፍትሕ ጥያቄ መልስ ለመስጠትም የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የመልዕክተኞች ጓድ ሳዑዲ አረቢያ ደርሶ ተመልሷል።

https://p.dw.com/p/2xBo4
Campaign to help Ethiopian boy in Jiddah
ምስል DW/N. Sirak

(Q&A) Campaign to help Ethiopian boy in Jiddah - MP3-Stereo

ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሐኪሞች ሥሕተት የሆስፒትል ቁራኛ የሆነዉን ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ወጣት እና ወላጆቹን ለመርዳት የጀመሩትን ዘመቻ እንቀደጠሉ ነዉ።ኢትዮጵያዉያኑ የእግር ኳስ ግጥሚያ እና የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት እስካሁን ሐምሳ ሺሕ ሪያል አዋጥተዋል።ኢትዮጵያዉያኑ ላነሱት የፍትሕ ጥያቄ መልስ ለመስጠትም የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የመልዕክተኞች ጓድ ሳዑዲ አረቢያ ደርሶ ተመልሷል።ታዳጊዉ ወጣት መሐመድ አብዱል አዚዝ በ4 ዓመቱ ለመለስተኛ ቀዶ ሕክምና  ሆስፒታል እንደገባ ሐኪሞች በፈፀሙት ሥሕተት ከሆስፒታል አልጋ ሳይላቀቅ አስራ-ሰወስት ዓመት አልፎታል።የጂዳ ወኪላችን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ