1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣትነት እና መፅሀፍ

ዓርብ፣ ሐምሌ 18 2006

ሁለት በመፅሀፍ ንግድ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ናቸው። አንዱ በአደባባይ ሌላኛዋ ደግሞ በኢንተርኔት መፅሀፎችን ለአንባቢዎቻቸው ያቀርባሉ። ስለሁለቱ ወጣቶች የመፅሀፍ ንግድ እና ከዚህ ጋር ሳይነሳ የማያልፈው የማንበብ ፍላጎት እና ባህል፤ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ምን እንደሚመስል አንድ የከፍተኛ ተቋም መምህርን ጠይቀናል።

https://p.dw.com/p/1CibU
Frau in Bibliothek
ምስል Fotolia/raeva

ጠዋት 2 ሰዓት ተኩል የመንገድ ዳር ሱቁን የሚከፍተው ጌታቸው ሳሙኤል ገና በልጅነቱ ነው ጋዜጣና መፅሄት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች መሸጥ የጀመረው።አሁን ደግሞ መጽሀፎችም ከመደብሩ አይጠፋም። ጌታቸው ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ላይ መፅሀፎቹን ለነሱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቆልፎ ወደ ቤቱ ሲያቀና የማርታ ኃይለእየሱስ ገበያ ግን ለ24 ሰዓታት ክፍት ነው። ማርታ እንደ ጌታቸው በመፅሀፍ ንግድ ነው የተሰማራችው። የሷ ንግድ በፌስ ቡክ ነው።

ማርታ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ባገኘችበት የገበያ አስተዳደር ሙያ በአንድ የግል መስሪያ ቤት ውስጥ ቀን ቀን ተቀጥራ ትሰራለች። ማታ ማታ ደግሞ በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የ3ኛ ዓመት የትያትር ተማሪ ናት። ይህን ጎን ለጎን የምትሰራውን የኢንተርኔት የመፅሀፍ ሽያጭ ለመጀመር እንዴት እንደተነሳሳች ገልፃልናለች። ወጣቷ ከ5 ወር በፊት የጀመረችው የመፅሀፍ ሽያጭ በደንብ ባይስፋፋም ጥሩ አስተያየት እያገኘችበት እንደሆነ ትናገራለች። ወጣቷ በስልክ ለሚደውልሏት ደንበኞች የምታቀርባቸውን መፅሀፎች የምታገኘውም በሁለት አይነት መንገድ ነው።

የወጣቱስ የማንበብ ፍላጎት ምን ይመስላል? በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የስነ ልሳን መምህር የሆኑት ዶክተር ዘላለም ልየው ከወጣቱ ጋ በእየዕለቱ ግንኙነት አላቸው። የታዘቡትን አካፍለውናል።

ለአንባቢያን በተለያዩ መንገድ መፅሀፍ ከሚያቀርቡት ጌታቸው ሳሙኤል ፣ማርታ ኃይለእየሱስ እና በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የስነ ልሳን መምህር ከሆኑት ዶክተር ዘላለም ልየው ጋር የነበረንን ቆይታ ከየወጣቶች ዓለም ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ