1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣትና ጎልማቾች በወላጅ ቤት ሲኖሩ

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2005

ወላጅ ቤት ሲኖር ለቤት ወጪ ብዙ ማሰብ አያስፈልግም፤ ኑሮ የተመቻቸ ነው የሚባለው ርግጥ ነው? ከወላጅ ቤት ወጥቶ ቤት ተከራይቶ መኖርስ ነፃነቱ ምን ያህል ነው?

https://p.dw.com/p/182Dc
Kinderheim Kids in Köln-Brück Foto: Victor Weitz / DW, 21.07.2011
ምስል DW/Weitz

በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በውጪውም አለም ከ18-34 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ በወላጆቻቸው ቤት የሚኖሩ ወጣት እና ጎልማሶች ቁጥር ጨምሯል።

ወጣት እና ጎልማሶች ራሳቸውን ችለው እንዳይኖሩ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ያለው የህብረተሰቡ ወይንም ያለመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን፤ ለአብዛኛው ወጣት እና ጎልማሳ የመተዳደሪያ እና የመኖሪያ ቦታ እጥረት ነው ሊባል ይችላል።

በዛሬው የወጣቶች አለም ከወላጆቻቸው ጋ እና ብቻቸውን የሚኖሩ ወጣት እና ጎልማሶች ያላቸውን ልምድ ነግረውናል።

በጎልምስና እድሜም ወላጅ ቤት ኖሮ ፤ዘግይቶ ራስን መቻል በስነ ልቦና ላይ ሚና ይጫወታል? ባህልሱ ራስን ችሎ የመኖሩን ሁኔታ ምን ያህል ያበረታታል?

ቀደም ሲል አንዲት ሴት የራሷ መተዳደሪያ ኖሯት ብቻዋን ቤት ተከራይታ ልኑር ብትል የህብረተሰቡስ አቀባበል እንዴት ነበር? በአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ የማህበራዊ ኑሮ ባለሙያ ( የሶሲዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር)- ዶክተር የራስ ወርቅ መልስ ሰጥተውናል። ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ