1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣትዋ ደራሲ

ዓርብ፣ ግንቦት 5 2008

ገና የ 21 ዓመት ወጣት ናት። በአንባቢ እጦት ይሁን፤ በህትመት ዉጣ ዉረድ የረዥም ልቦለድ መጻሕፍት እየቀነሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ወደ 300 ገጾች ግድም የሚሆን ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርባለች

https://p.dw.com/p/1InXY
Briefpapier Tinte
ምስል Fotlia/rsester

ወጣትዋ ደራሲ


ደራሲ «ሰብለወንጌል ፀጋ» ነዋሪነትዋን ሃዋሳ ከተማ ያደረገችዉ ወጣትዋ ደራሲ ሰብለወንጌል ፀጋ የተወለደችዉ በባሌ ዞን ጎባ ከተማ ዉስጥ ሲሆን ቤተሰቦችዋ በሥራ ምክንያት ወደ አርሲ ነገሌ ሲዘዋወሩ አብራቸዉ እየተዘዋወረች የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትዋን ካጠናቀቀች በኋላ በ 2007 ዓ,ም በመቀሌ ዩንቨርስቲ በአካዉንቲንግ እና ፋይናንስ በዲግሪ ተመርቃለች። በዩንቨርስቲ ቆይታዋ «መጽሐፉ» የተሰኘ የመጀመርያ መጽሐፍዋን አሳትማ አቅርባለች። ወደ መጽሐፉ ይዘት ከመግባታችን በፊት ሰብለወንጌልን በሕጻንነትዋ ስለነበራት የሥነ-ጽሑፍ ዝንባሌ እንድትነግረን ጠይቀናት ነበር።
« እንደምክንያትነት የምቆጥረዉ ቤተሰባችን ዉስጥ ታላቅ እህቴ ብዙ መጽሐፍትን ታነባለች። በዝያ ምክንያት ብዙ መጽሐፍት ነበሩን። እነዚህ መጽሕፍት ደግሞ ከኔ እድሜ ጋር የማይመጣጠኑ ስለነበሩ እህቴ እንዳላነባቸዉ ትደብቅብኝ ነበር። ግን የስዋን መጽሐፍቶች እየፈለኩኝ ከተደበቀበት እያወጣሁ አነብ ነበር። በሌላ በኩል የተሰማኝን ስሜት የመጻፍ ልምዱ አለኝ፤ ማለት ሲከፋኝ ወይም ስደሰት ለሰዉ ከመንገር ይልቅ የመጻፍ ልምድ አለኝ። ይህ ልምድ ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ያለ ነዉ። እናም እያነበብኩ አደኩ ከዝያ በኋላ ነዉ እንደዚህ አጫጭር ነገሮችን የፈጠራ ጽሑፎችን መጫጫር ጀመርኩ እና እሱ ነዉ እያደገ የመጣዉ።»
የእለቱ የወጣቶች ዝግጅት የ 21 ዓመቷን ወጣት ደራሲ ሰብለወንጌል ፀጋን ያስተዋዉቀናል፤ ሙሉ ቅንብሩን ተከታተሉ


ዮኃንስ ገ/እግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ