1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ አሳሳቢዉ የግድያ፣ የዘረፋና የአፈና ወንጀል በኢትዮጵያ  

እሑድ፣ ሰኔ 9 2011

ተወያዮች «በሃገሪቱ ያለሥጋት ወጥተን በሰላም መግባት ማደር አለብን። ይህን ማስፈፀም የመንግሥት ኃላፊነት ነዉ። ሌላዉ ሌላዉ ችግር መፍታት በመጀመርያ ደህንነት ሲረጋገጥልን ነዉ። በህይወት መኖር አለንብ። ሥጋት ዉስጥ ነዉ ያለነዉ። መንግሥት የያዘዉን ነገር ቢፈትሸዉ ጥሩ ነዉ። መሰረታዊዉ ችግር ግን፤ ረዘም ላሉ ዓመታት የተጠራቀሙ ችግሮች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/3KXNC
Symbolbild Justiz Gericht Richterhammer
ምስል picture alliance/imageBROKER

«የብዙ ችግሮች ድምር ደህንነታችንን አናግቶታል» ተወያዮች

ኢትዮጵያ ዉስጥ በፖለቲካ ልዩነትና  ማንነት ላይ  መሰረት ባደረጉ ግጭቶች  ሳብያ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል በርካቶችም ለአካል ጉዳትና ለሞት ተዳርገዋል። ከጥቂት ወራቶች ወዲህ ይህ ግጭትና መፈናቀል የቀነሰ ቢመስልም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች  በተናጠል ዘረፋ እንደተፈፀመባቸዉ የሚናገሩ አሉ። በተለያዩ አካባቢዎች በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በተካሄዱ የዉይይት መድረኮችም «በሰላም ወጥቶ መግባት» አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ሲገልፁ ታይቶአል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል አዲስ አበባ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ከሳምንት በፊት ደግሞ ተቀማጭነቱን እዚያዉ አዲስ አበባ ያደረገዉ የአፍሪቃ ሕብረት የጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዘርፍ ባወጡት መግለጫ፤ አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉን የወንጀል ድርጊት በመግለጽ ሰራተኞቻቸዉ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ መክረዋል። በሌላ በኩልም ወላጆች  በድህነት አሳድገው ለወግ ለማዕረግ ይበቃሉ፤ የሀገር ተስፋ ይሆናሉ፤ ያሉዋቸው ልጆቻቸው፤በዩንቨርስቲዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ሕይወታቸዉ የሚያልፍ ተማሪዎች ጉዳይም አሳሳቢ እየሆነ መጥቶአል። ያም ሆኖ ግን  የድርጊቱ  ፈጻሚዎች በአፋጣኝ ሕግ ፊት ሲቀርቡ ባለመታየታቸዉ ሁኔታዉ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄና  ቅሪታ እየፈጠረ መቶአል።  አሳሳቢዉ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ እና ችግሩ ብሎም መፍትሄው ምን ይሆን?

በተወያዮች አስተያየት፤ «በሃገሪቱ ያለሥጋት ወጥተን በሰላም መግባት ማደር አለብን። ይህን ማስፈፀም የመንግሥት ኃላፊነት ነዉ። ሌላዉ ሌላዉ ችግር መፍታት በመጀመርያ ደህንነት ሲረጋገጥ ነዉ። በህይወት መኖር አለንብ። በሕግ ጥላ ሥር መኖር አለብን። ስጋት ከላያችን ሊገፈፍ ይገባል። አሁን እየኖር ያለነዉ በሥጋት ዉስጥ ነዉ። መንግሥት የያዘዉን ነገር ቢፈትሸዉ ጥሩ ነዉ። መሰረታዊዉ ችግር፤ ረዘም ላሉ ዓመታት የተጠራቀሙ ችግሮች ለአሁኑ የደሕንነት ማጣት ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። የሕዝብ ቁጥር በተለይ የወጣቱ ቁጥር መጨመር፤ ብሎም ጥራት ያለዉ ትምህርት ያለማግኘት። ሃገሪቱ ዉስጥ የመዋቅር ለዉጥ አለመምጣት፤ የግብርናዉ አለመዘመን፤ የኢንዱስትሪዎች አለመስፋፋት፤ የመንግሥት ተጠሪዎች በአብዛኛዉ በሙስና በመዘፈቃቸዉ፤ ፖለቲካዉ በዘር ፖለቲካ መዋጡ እና የወንጀል መደበቅያ መሆኑ ነዉ። የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ድምር ድህነት በማስከተሉ፤ ግድያ ዝርፍያ እና አፈና እየተበራከተ መጥቶአል። ሌሎች በበኩላቸዉ፤ በሃገሪቱ የፀጥታ አካላት አይነት መብዛቱ ፤ጥልቅ የሆነ ሰብዓዊነትን እና ፍትህን ያማከለ ጥናት ባለመዉሰዳቸዉ፤ ለዉጡን ለማምጣት የታገሉት ወጣቶች ፤ ሕጋዊ የሆነ ተጠያቂ ማኅበር ዉስጥ ባለመደራጀታቸዉ ነዉ። በሕዝባዊ አመጽ የመጣዉ ለዉጥ ፤ በግዴታ በመምጣቱ አሁን ግልፅ የሆነ የለዉጥ መንገድ  ገብተናል። ሲሉ ሃሳብ ሰንዝረዋል።»

በዉይይት አስተያየታቸዉን ሊያካፍሉን፤ መስከረም አበራ፤  የአዋሳ ዩንቨርስቲመምህርት እንዲሁም የፖለቲካ ሃያሲ፤ አንጋፋዉ  የህግ ባለሙያና ተንታኝ ሞላ ዘገየ ፤ አቶ ሚኑኖስ ሁንዱራ ፤ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች በመምህርነት የሚያገለግሉና  በፌደራሊዝም ዴሞክራሲና ልማት ላይ ጥናት በማካሄድ ድረግ ላይ የሚገኙ፤ እንዲሁም አቶ አንተነህ ተስፋሁን በባህርዳር ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና ተንታኝ ናቸዉ። ተወያዮች በዉይይቱ ቀርበዉ ኃሳባቸዉን ስላካፈሉን በማመስገን ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።  

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ