1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ የካቢኔ ሹም ሽርና የሕዝብ ጥያቄ

ነጋሽ መሐመድ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 16 2009

መንግሥት ለማሻሻል ወይም ለመለወጥ ቃል የገባቸዉ ሕግጋት፤አወቃቀሮች፤ ድርድር፤ የሥራ ፈጠራዎች ምንነት፤ጥቅም-ጉዳታቸዉ ወይም የገቢራዊነታቸዉ መዘግየት ብዙ ማነጋገሩ አይቀርም።ለዛሬ ለመነጋገሪያ ርዕስነት የመረጥነዉ ግን የተጀመረ ወይም የተጠናቀቀዉን የካቢኔ ሹም ሽሩን ነዉ።የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ መጥቀም-አለመጥቀሙን እንቃኛለን።

https://p.dw.com/p/2Uokp
Äthiopien Addis Abeba Vereidigung Kabinett
ምስል Imago/Xinhua

ዉይይት፤ የካቢኔ ሹም ሽርና የሕዝብ ጥያቄ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ፤ ጥያቄና ቅሬታ ለማስወገድ ወይም ለመመለስ ከወሰደና ከሚወስደዉ የሐይል እርምጃ በተጨማሪ ፖለቲካዊ፤ ሕጋዊ፤ ኤኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ መፍትሔዎች ያላቸዉን እርምጃዎች እንደሚወስድ አስታዉቋል።መንግስት ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር መደራደር፤ ተቃዋሚዎችን በአንዳድ ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ማሳተፍ ያለዉ ሐሳቡ ከፖለቲካዊዉ ዕቅድ የሚጠቀሰዉ ነዉ።ከሕጉ መስክ የምርጫ ደንብ ለማሻሻልና የምርጫ ቦርዱን  ለመለወጥ ማስታወቁ ዋናዎቹ ናቸዉ።ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የገባዉ ቃልም አለ።

እስካሁን  አነሰም በዛ ገቢራዊ ማድረግ የጀመረዉ ግን አስተዳደራዊዉ ለዉጥ ነዉ።የፌደራላዊዉን መንግሥት ጨምሮ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በሚያስተዳድራቸዉ በትግራይ፤በአማራ፤በኦሮሚያ ፤በደቡብ  እና በአዲስ አበባ መስተዳድሮች ሹማምንቶች ተሽረዉ «ዶክተሮች በርከትከት» ያሉባቸዉ ካቢኔዎች ባዲስ መልክ ተሰይመዋል።

አዜብ ታደሰ