1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዋዴ ሲ ኤል ዊልያምስ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2005

የጀርመን የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት ፣ለልማት ፖለቲካ ና ለሰብዓዊ መብቶች ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ ጋዜጠኞች ተሰጥቷል ።

https://p.dw.com/p/19Q3Q
Portraitfoto Wade C.L.Williams Foto: Copyright Foto: Glenna Gordon Beschreibung: Portraitfoto der Journalistin Wade C.L. Williams, Teilnehmerin des Deutschen Medienpreis Entwicklungspolitik 2013, Gewinnerin der Region Afrika. Foto: Glenna Gordon
ምስል Glenna Gordon

በምርጫው ሂደት ትኩረት የተሰጣቸው ስኬታማ ና ያልተሟሉ እንዲሁም አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች ናቸው ። ሸላሚዎቹም ዶይቸ ቬለ እና የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴር BMZ ሲሆኑ ተሸላሚዎቹም ከአፍሪቃ፣ ከእስያ፣ ከላቲን አሜሪካ ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ፣ ከምስራቅ አውሮፓ እና ጀርመን የተውጣጡ ጋዜጠኞች ናቸው ።
እጎአ ከ 1975 ዓም ጀምሮ የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴር BMZ ሚዛናዊ ዘገባ ለሚያቀርቡ የጀርመን ጋዜጠኞች ሽልማት ሲሰጥ ቆይቷል ። በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ BMZ ከዶይቸ ቬለ ጋ በመተባበር የሰጠው የዚህ ሽልማት አሸናፊ የላይቤራዊቷ ጋዜጠኛ የዋዴ ሲ ኤል ዊልያምስ „ Still a hard life „ በሚል ርዕስ የተፃፈው ታሪክ ነው ።
ዋዴ ሲ ኤል ዊልያምስ በሀገሯ በላይቤሪያ በአብዛኛው ለሴቶች ዝግ በሆነውና አደገኛነቱ በሚያመዝነው በጋዜጠኝነት ሙያ ከፍተኛ እውቅና አትርፋለች ። መርማሪ ጋዜጠኛዋ ዊልያምስ ፣ በዋና ከተማዋ በሞንሮቭያ የሚታተመው « ፍሮንት ፔጅ አፍሪቃ» የተባለው ጋዜጣ እና የኢንተርኔት ድረ ገጽ የዜና ክፍል ሃላፊም ናት ። ጋዜጠኛዋ የላይቤሪያውን ርስ በርስ ጦርነቱን በቅርብ ታዝባለች ። የምትፅፋቸው ፁሁፎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስቆጥቷል ። ስለ ሴት ልጅ ግርዛት በመፃፉዋም የግድያ ዛቻ ሳይቀር ተሰንዝሮባታል ። አለቃዋ ሀገሪቱን ለመልቀቅ ሲገደድም ዊልያምስ የጋዜጣው ህትመት እንዲቀጥል አድርጋለች ። የጋዜጠኛዋ ቁርጠኝነትና ፅናት ታዋቂ አድርጓታል ። በስራዋ ብዙ ሽልማቶችን ያገኘችው የዊሊያምስ ፁሁፎች እንደ ብሪታኒያው ጋርድያን ባሉ ዓለም አቀፍ ጋዜጦች ላይ በድጋሚ ለመታተም በቅተዋል ።
በዚህ አመት ለሽልማት ያበቃት ፁሁፍ ሴት መሪ ባላትና የሴቶችንም ህይወት ለማሻሻል ብዙ ቃል በተገባባት በላይቤሪያ በርካታ ሴቶች እና ልጃገረዶች እስካሁን ድረስ እንዴት በድህነት እንደሚኖሩ ያወጋል ። "Still a hard life" የተሰኘው ይሄው ጹሁፍ ሜርሲ ዎሜህ የተባለች ወጣት ልጃገረድ ከድንጋይ ጠረባ በምታገኘው ገንዘብ የትምህርት ቤት ወጪዋን ለመሸፈን የምታደርገውን ትግል ይዘረዝራል ። ድንጋይ ጠረባ በሃገሪቱ ገንዘብ ማግኘት ከሚያስችሉ ጥቂት መንገዶች አንዱ ነው ። ምንም እንኳን ላይቤሪያ 9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም ከሕዝቧ 85 በመቶው ስራ አጥ ነው።

ፁሁፉን ለማንበብ "Still a hard life: Despite female leader, Liberian women still crush rocks"