1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዌሊንግተን ኒውዚላንድ ዉስጥ አንድ ታጣቂ 49 ሰው ገደለ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011

ኒውዚላንድ ውስጥ አንድ ታጣቂ በሁለት መስጊዶች ላይ ዛሬ በከፈተው ተኩስ 49 ሰዎችን ገድሎ ከ40 የሚበልጡትን ደግሞ አቆሰለ። ሮይተርስ እንደዘገበው ታጣቂው የተኮሰው ለአርብ የጁማ ስግደት መስጊዶቹ ውስጥ በሚካሄደው የጸሎት እና ስግደት ስነ ስርዓት ላይ በታደሙ ሰዎች ላይ ነበር።

https://p.dw.com/p/3F9aZ
Neuseeland Anschlag in Christchurch
ምስል Reuters

ኒውዚላንድ ውስጥ አንድ ታጣቂ በሁለት መስጊዶች ላይ ዛሬ በከፈተው ተኩስ 49 ሰዎችን ገድሎ ከ40 የሚበልጡትን ደግሞ አቆሰለ። ሮይተርስ እንደዘገበው ታጣቂው የተኮሰው ለአርብ የጁማ ስግደት መስጊዶቹ ውስጥ በሚካሄደው የጸሎት እና ስግደት ስነ ስርዓት ላይ በታደሙ ሰዎች ላይ ነበር። ጥቃት አድራሹ በተለይ ክራይስትቸርች በተባለው ከተማ በሚገኝ አንድ መስጊድ ሲሄድ እና ገብቶም በእሩምታ ተኩስ ሲከፍት የሚያሳይ ቪድዮ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ለቋል ተብሏል። በዚሁ ቪድዮ ላይ የሞቱ ወይም የቆሰሉ ሰዎች ወለል ላይ ወድቀው ይታያሉ።  ጥቃት ከተፈጸመበት አልኑር በተባለው መስጊድ እንደነበረ የተናገረ አንድ ሰው ታጣቂው ነጭ ባለ ወርቃማ ጸጉር እና ጭምብል እና የጥይት መከላከያ ሰደርያ ያጠለቀ እንደነበር ገልጿል። መስጊዱን በርግዶ ሲገባም ምዕመናኑ ተንበርክከው ነበር ብሏል። የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በኒውዚላንድ በዓይነቱ የመጀመሪያ የተባለውን ይህን ጥቃት አውግዘው ድርጊቱንም አሸባሪነት ብለውታል። ፖሊስ በግድያ የተጠረጠውን እድሜው በ20 ዎቹ መጨረሻ የሆነውን ወጣት ጨምሮ 3 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ዋነኛው ተጠርጣሪ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሏል። ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ማንነት ይፋ አላደረገም። 

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ