ዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መደረክ ተጠናቀቀ28 ግንቦት 2001ዓርብ፣ ግንቦት 28 2001ዶቼ ቬለ ያዘጋጀዉ ለሦስት ቀናት የዘለቀዉ ዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ዛሬ ተጠናቀቀ። ከአንድ መቶ አገራት የተዉጣጡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን ያገናኘዉ ይህ ጉባኤ በበዘርፈ ብዙ የመገናኛ ብዙሃን ጠቀሜታ ዙሪያ ተወያይቷል።https://p.dw.com/p/I4Clኤሪክ ቤተርማን የዶቼ ቬለ ሥራ አስኪያጅማስታወቂያበጋዜጠኝነት አዘጋገብ ወዳጅ ጠላት የሚባል መኖር የለበትም በሚለዉ የዉይይት ነጥብም ግጭትን ከማባባስ መቆጠብ ከሙያዉ ስነምግባር ዋነኛዉ መሆኑ ተመልክቷል። ከጉባኤዉ ተሳታፊዎች መካከል በዘመናዊዉ ቴክኒዎሎጂ ማለትም ኢንተርኔት ንዑሳን ገፆች ላይ ማኅበረሰባቸዉን የሚጠቅም ተግባር የፈፀሙ ድንበር አልባ ጋዜጠኞች የሚል ሽልማት ከዶቼ ቬለ ተበርክቶላቸዋል። ሸዋዬ ለገሰ/ተክሌ የኋላ