1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓረና ትግራይ በታቀደው ምርጫ አልሳተፍም አለ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2012

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ በክልሉ ሊደረግ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ፡፡ ዓረና በትግራይ ሊደረግ የታቀደው ምርጫ ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ሲል ገልፆታል፡፡ዓረና ትግራይ የክልሉ መንግስት እያደረገ ያለው የምርጫ እንቅስቃሴ አቁሞ ትኩረቱ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

https://p.dw.com/p/3g3r2
Äthiopien Arena Tigray, Opposition
ምስል DW/M. Hailessilassie

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ በክልሉ ሊደረግ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ፡፡ ዓረና በትግራይ ሊደረግ የታቀደው ምርጫ ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ሲል ገልፆታል፡፡ በትግራይ ተመስርቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ 12 ዓመታት ያለፉትና ባለፉት ሁለት ሀገራዊ ምርጫዎች የተሳተፈው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ዘንድሮ በትግራይ ሊካሄድ ከታቀደው ምርጫ ራሱን ማግለሉ ያስታወቀው በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ 'ዓረና ነፃ፣ ፍትሓዊና ሕገ መንግስታዊ ባልሆነ ምርጫ አይሳተፍም' በሚል ርእስ ስር ባወጣው መግለጫ እንደጠቆመው በነፃነት የተደራጀ ሲቪክ ማሕበራት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ሚድያዎችና ሌሎች ተቋማት በሌሉበት በትግራይ ፍትሓዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ እንደማይታሰብ አስታውቋል፡፡ የዓረና ትግራይ ቃል-አቀባይ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ "በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ምርጫ በገለልተኛና ሕጋዊ ተቋም መመራት ሲገባው፡ በአንድ ገዢ ፓርቲ ውሳኔ ወደ ምርጫ መግባት ዓረና አይቀበለውም" ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዓረና ትግራይ የክልሉ መንግስት እያደረገ ያለው የምርጫ እንቅስቃሴ አቁሞ ትኩረቱ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ