1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘላቂነቱ ያላስተማመነው የቡርኪና ፋሶ ፀጥታ

ቅዳሜ፣ መስከረም 15 2008

የቡርኪና ፋሶ በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሃገር ቡርኪና ፋሶ የመፈንቅለ መንግሥቱ በይፋ ካበቃ ቀናት ተቆጥረዋል። የስልጣን ሽኩቻው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከስልጣን የተባረሩት የቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ብሌዝ ካምፓዎሬ ደጋፊዎች አሁንም ከስልጣኑ መድረክ ለመራቅ የፈለጉ አይመስልም።

https://p.dw.com/p/1Ge1C
Burkina Faso Ouagadougou Präsidentenpalast
ምስል picture-alliance/dpa/L. Koula

ትኩረት በአፍሪቃ፤ ዘላቂነቱ ያላስተማመነው የቡርኪና ፋሶ ፀጥታ

የሽግግሩ መንግሥት ግን ይህን ለማከላከል ነው ጥርት የጀመረው። እርግጥ፡ የመፈንቅለ መንግሥቱ አራማጆች ስልጣኑን ከአንድ ዓመት በፊት ለተመሸረተው የሽግግር መንግሥት ከጥቂት ቀናት በፊት ካስረከበ ወዲህ ቡርኪና ፋሶ የተረጋጋች ትመስላለች፡ የፖለቲካ ተንታኞች ግን በሃገሪቱ ሁከቱ እንደገና ሊነሳ የሚችልበት ስጋት ከፍተኛ መሆኑን ነወ ያስጠነቀቁት። የሃገሪቱ የወደፊት እጣ ምን ሊመስል እንደሚችል ጠብቆ የሚታይ እንደሚሆን ትንታኞች አመልክተዋል።

አርያም ተክሌ
ልደት አበበ