1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘረኛነት በሊባኖስ

ዓርብ፣ ነሐሴ 7 2002

በሊባኖስ በቆዳ ቀለም ልዩነት የተነሳ ገደቦችና ክልከላዎች እንዳሉ አንድ ጥናት አመለከተ።

https://p.dw.com/p/OnS6
ዘረኛነት በሊባኖስ
ምስል AP

በተለይም ጥቁሮች ወደ መዝናኛ ሥፍራዎች እንዳይገቡ እንደሚደረጉ በጥናቱ ተመልክቷል። ኢንዲ አክት የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በካሄደው በዚሁ ጥናት ቤሩት ውስጥ በሚገኙ 20 የመዝናኛና የመዋኛ ሥፍራዎች ድርጊቱ ይከሰታል። የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ዓሊ ፋከሪ እንደሚሉት በዚሁ በቆዳ ቀለም ልዩነት የተነሳ ክልከላው የሚደረጋባቸው ከፊሊፒንስ፤ ከሲሪላንካ፤ ከኔፓልና ከኢትዮዽያ በመጡ የቤት ሠራተኞች ላይ ነው።v

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ