1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በዙማ ላይ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 24 2009

ድምፅ የሚሰጠው የሀገሪቱ የፀረ ሙስና መስሪያ ቤት ያቀረበው ሪፖርት ይፋ ከሆነ በኋላ ዴሞክራቲክ አልያንስ የተባለው የደቡብ አፍሪቃ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ዛሬ በዙማ ላይ የመታመኛ ድምጽ እንዲሰጥ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ነው ።

https://p.dw.com/p/2S6sU
Südafrika Tausende protestieren vor Präsidentenpalast gegen Zuma
ምስል Reuters/M. Hutchings

Beri .Johannesburg (Zuma's corruption crisis) - MP3-Stereo

የደቡብ አፍሪቃ ፓርላማ የተለያዩ የሙስና ክሶች በቀረቡባቸው የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ ላይ በመጪው ሳምንት የመታመኛ ድምጽ ሊሰጥ ነው ። ድምፅ የሚሰጠው የሀገሪቱ የፀረ ሙስና መስሪያ ቤት ያቀረበው ሪፖርት ይፋ ከሆነ በኋላ ዴሞክራቲክ አልያንስ የተባለው የደቡብ አፍሪቃ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ዛሬ በዙማ ላይ የመታመኛ ድምጽ እንዲሰጥ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ነው ። በርካቶችአደባባይ በመውጣት ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል ። ዙማ ከዚህም ቀደም ሁለት ጊዜ  የመተመኛ ድምፅ ማለፍ ችለዋል ።የጆሀንስበርጉ ወኪላችን መላኩ አያሌው ዝርዝር ዘገባ አለው ።
መላኩ አያሌው
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ