1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዚምባቡዌ፤ ሙጋቤና የኮሌራ ወረርሽኝ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2001

በዚምባቡዌ የሚታየዉ የምጣኔ ሃብት ቀዉስና የኮሌራ ወረርሽኝ በእሳቸዉ ምክንያት ሳይሆን በቀድሞ ቅኝ ገዢ ብሪታኒያ መዘዝ የተከሰተ መሆኑን ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ገለጡ።

https://p.dw.com/p/GLPr
...የተገኘዉ ይጠጣል
...የተገኘዉ ይጠጣልምስል AP
የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ ባለፈዉ ያካሄደዉን ዓመታዊ ጉባኤ ቅዳሜ ዕለት ሲያጠናቅቅ ይህን መሰሉን መልዕክት ያስተላለፉት ሙጋቤ እግረ መንገዳቸዉንም ከስልጣን የመዉረድ ሃሳብ እንደሌላቸዉ አመላክተዋል። በአገሪቱ የተከሰተዉ የኮሌራ ወረርሽኝ ብዙዎችን እየገደለ ባለበት በዚህ ወቅት ሙጋቤ ከእሱ ይልቅ ትኩረታቸዉን የጋለዉ የፖለቲካ ዉጥንቅጥ ላይ ማድረጋቸዉ አስተችቷቸዋል።