1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዛሬ የተጠናቀቀዉ የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥቅምት 10 2010

የአዉሮጳ ኅብረት ለሁለት ቀናት ያካሄደዉ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ተጠናቀቀ። ትናንት የተጀመረዉ የኅብረቱ መሪዎች ስብሰባ ስደት ዋነኛ መነጋገሪያዉ እንደነበር ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/2mGIa
Belgien EU-Gipfel
ምስል Reuters/V. Mayo

የስደተኞች ጉዳይ ዋነኛ መነጋገሪያ ነበር፤

ተሰብሳቢዎቹ በዉይይታቸዉ ወቅት የኅብረቱን የዉጭ ድንበር የመቆጣጠሩ ርምጃ ወደአዉሮጳ ዘልቀዉ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር መቀነስ ማስቻሉን አመልክተዋል። ከዚህም ሌላ በብሪታንያ ከአባልነት የመዉጣት ሂደት ላይ የተነጋገሩ ሲሆን፤ ከኢራን ጋር የተደረሰዉ የአቶም መርሃግብር ስምምነትን አፅንተዉ እንዲሚቀጥሉም አዉስተዋል። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ