1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝክረ-ድሬስደን

ማክሰኞ፣ የካቲት 6 2004

የካቲት አምስት ቀን ለጀርመኗ ድሬስደን ከተማ መቼም የማይረሳ ቀን ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጥምሩ ሀይል ከተማዋን ከአውሮፕላን በተወረወሩ ቦንቦች ድምጥማጧን ያጠፋበት ዕለት። ያ ከተከሰተ ታዲያ 67 ዓመታትን አስቆጥሯል።

https://p.dw.com/p/143Kw
የ2ኛው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ በድሬስደን ከተማ
የ2ኛው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ በድሬስደን ከተማምስል AP

እ. ኤ. አ. 1945 ዓ.ም. ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል። ወርሀ-የካቲት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት በጥምሩ ሀይል ድል ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቢቀሩት ነው። በድሬስደን ከተማ ሰማይ ላይ የጥምሩ ሀይል የጦር ጀቶች እየተመላለሱ ነው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከተማዋ ላይ ያወረዱት የቦንብ ናዳ ከተማዋን እንዳልነበረች ያደርጋታል። ከአውሮፕላኖቹ የሚወረወሩት ቦንቦች ግዝፈት አይጣል ነበር። የድሬስደን ነዋሪዎች ከተማቸው በ15 ደቂቃዎች ውስጥ በቦንብ ውርጅብኝ እንዳልነበረች ሆና ዶግ አመድ የሆነችበትን ያቺን ቀን ከግማሽ ምዕተ- ዓመታት በላይ ከዓመት ዓመት ሲዘክሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። በዛች መከረኛ ምሽት ከ20.000 በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከአመዱ ውስጥ ተቀብረው ቀርተዋል። መፍቀሬ ናዚ ቀኝ አክራሪዎች ዕለቱን ለቅስቀሳ በመጠቀም ወደዚችው ከተማ መጉረፉቸውን ግን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሂሩት መለሰ