1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዠኔቭ፣ የመን እና የለጋሽ ሀገራት ጉባዔ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2009

የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉተረሽ እና የበርካታ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በርስ በርስ ጦርነት በደቀቀችው የመን የተከሰተውን  ሰብዓዊ ቀውስ ለመቀነስ የሚያስችል ድጋፍ ለማሰባሰብ ዛሬ በዠኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ጉባዔ አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/2bujp
UN Geberkonferenz Jemen in Genf Guterres, Wallstrom und Burkhalter
ምስል picture-alliance/AP Photo/V. Flauraud

የተመድ፣ ስዊትዘርላንድ እና ስዊድን በጋራ ባስተናገዱት በዛሬው ጉባዔ እጎአ በ2017 መጀመሪያ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለየመን ለመስጠት ቃል ከገባው የ2,1 ቢልዮን ዩኤስ ዶላር ርዳታ መካከል 1,1 ቢልዮኑን እንደሚያቀርብ ዋስትና ለማግኘት ተችሏል። የተመድ የአስቸኳይ ርዳታ አስተባባሪ መስሪያ ቤት፣ በምህፃሩ «ኦቻ» እንዳስታወቀው ፣ በየመን በወቅቱ 18,8 ሚልዮን ሰው አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ያስፈልገዋል።  ወደ 2,2 ሚልዮን የሚሆኑ ሕፃናትም ባልተመጣጠነ አመጋገብ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ በየአስሩ ደቂቃም የአንድ ሕፃን ሕይወት ያልፋል። እጎአ ከ2015 ዓም ወዲህ በቀጠለው የርስበርሱ ጦርነትም እስካሁን ከ10,000 የሚበልጥ ሰው የተገደለ ሲሆን፣ ወደ ሶስት ሚልዮን የሚጠጉ ተፈናቅሏል። 

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ