1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀዋሳ ከተማ 50ኛ ዓመት ምስረታ

ሐሙስ፣ ኅዳር 16 2003

የደቡብ ብሔር ብሔሮችና ህዝቦች ክልል መዲና ሀዋሳ የተቆረቆረችበትን 50ኛ ዓመት ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረች ነው።

https://p.dw.com/p/QI0X
የሀዋሳ ከተማ 50ኛ ዓመት ምስረታ

ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን ትጠቀሳለች። የተለያዩ የኢትዮዽያ ብሄረሰቦች መኖሪያ በመሆኗም ስብጥር ገጽታ ጎልቶ ይታይባታል። ከሌሎች አቻ የኢትዮዽያ ከተሞች አንጻር ዕድሜዋ ትንሽ ቢሆንም ዕድገቷ የፈጠነ ነው። ታዲያ ሀዋሳ ከተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የተላቀቀች አይደለችም። ገና ብዙ ይቀራታል ይላሉ ያይዋት። መሳይ መኮንን ከተማዋን የቆሮቆሩትንና በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑትን ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ጨምሮ የከተማዋን ኃላፊዎች አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ