1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 11 2010

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶች ያስከተሏቸዉ የሕይወት መጥፋት እና መፈናቀል የዜጎችን ትኩረት ከሳበ ዉሎ አድሯል። ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃኑ ዛሬም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ ለተቃዉሞ አደባባይ መዉጣታቸዉን ይጠቁማሉ።

https://p.dw.com/p/2pimn
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

ዋና ከተማ አዲስ አበባ

 የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲም በስብሰባዎች እንደተጠመደ ነዉ ። ከመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን  ማግኘት የተሳነዉ ሕዝብ  ስጋት እንደተሰማዉ፤ በጊዜም ወደየቤቱ መከተት መጀመሩ ይሰማል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን ይላሉ? የከተማዋ መገናኛ ዘዴዎችስ? ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን  ሸዋዬ ለገሠ በአጭሩ በስልክ አነጋግራዋለች።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

 ሸዋዬ ለገሠ