1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገር ባህል አልባሳት

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2005

በተቻላቸው መንገድ የባህል ልብሶችን በዘመናዊ እና ዕለት ከለት እንዲለበሱ አድርገው ለማቅረብ እንደሚጥሩ ሁለት በባህል ልብስ ስፌት ላይ ያተኮሩ የባህል ዝግጅት ተሳታፊዎች ይገልፃሉ።

https://p.dw.com/p/17oJx
Mannequin: Schaufensterpuppen in Bonn, Deutschland; Copyright: DW/M. Mohseni
ምስል DW/M. Mohseni

ዘመናዊ የባህል ልብሶች አሁን አሁን በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይበልጥ እየተዘወተሩ ነው። እነዚህን አልባሳት ለገበያ ከሚያቀርቡ የልብስ ሰፊዎች( ዲዛይነር) መካከል ሰላማዊት ታደለ አንዷ ናት። ድሮ የልብስ ስፌት በትርፍ ጊዜዋ ነበር የምትሰራው። አሁን ግን የነርስ ሙያዬን ትቼ ሙሉ በሙሉ በባህል ልብስ ቅድ ስራ ልገባ ነው የምፈልገው ትላለች የ27 አመቷ ሰላማዊት። ከዚህ ቀደም የተለመዱት የባህል ጥበብ ቀሚሶችን እንደ ምሳሌ ብንወስድ፣ ነጫጭ ፣እና ሰፋ ያሉ ነጠላ ያላቸው ናቸው። ሰላማዊት በነዚህ ብቻ መወሰን አትፈልግም። እሷ ብቻ አይደለችም

ወ/ት ቅድስት ሙሉጌታም እንደ ሰላማዊት የባህል ልብሶችን ትሰፋለች። በልብስ ቅድ ስራ ከ 10 አመት በላይ ሆኗታል። የሀገር ባህል አልባሳትን በዘመናዊ መልኩ ለማቅረብ ያነሳሱዋት ምክንያቶች አሉ።

የሀገር ባህል አልባሳትን አዘውትሮ ስለመልበስ ፍላጎት እና ከዛ ጋ የተያያዙ ፈተናዎችን በተመለከተ የባህል ዝግጅት ተሳታፊዎች ያጫወቱን አለ። ከድምጽ ዘገባው ታገኙታላችሁ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ