1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለተኛው ትልቁ ማክሰኞ ምርጫ ውጤት በአሜሪካ

ረቡዕ፣ መጋቢት 7 2008

ትናንት በ5 ወሳኝ ፌደራዊ ግዛቶች በተካሄደ ምርጫ ከዴሞክራት ፓርቲ ሂለሪ ክሊንተን ከሪፐብሊካኖች ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ አሸንፈዋል ።

https://p.dw.com/p/1IEBf
USA Vorwahlen in Florida Hillary Clinton in West Palm Beach
ምስል Getty Images/J. Raedle

[No title]

በመጪው ጥቅምት መጨረሻ ለሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራትና የሪፐብሊካን ፓርቲዎችን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች የመለያ ምርጫ ፉክክሩ ቀጥሏል ። ትናንት በ5 ወሳኝ ፌደራዊ ግዛቶች በተካሄደ ምርጫ ከዴሞክራት ፓርቲ ሂለሪ ክሊንተን ከሪፐብሊካኖች ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ አሸንፈዋል ። ቅዳሜ ሳይጠበቅ በተቀናቃኛቸው በርኒ ሳንደርስ በሚሽጋን የተሸነፉት ሂለሪ ክሊንተን ትናንት በፍሎሪዳ ኦሃዮ ኤሊኖይስና ኖርዝ ካሮላይና ፌደራዊ ግዛቶች አሸንፈዋል። ዶናልድ ትራምፕም በፍሎሪዳ በኖርዝ ካሮላይናና በኤሊኖይስ ድል ቀንቷቸዋል። በኦሃዮ ግን ተሸንፈዋል ። ቆጠራው ባልተጠናቀቀው በሚዙሪ ደግሞ ክሊንተን እየመሩ ነው ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ልኮልናል ።

ናትናኤል ወልዴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ