1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁዳዴ ጾምና፣ የጾም ምግቦች

ሐሙስ፣ መጋቢት 8 2003

የምስር የሽሮ ወጥ፣ የተልባ የሱፍ ፍትፍት፣ የሽንብራ አሳዉ፣ እልበት ስልጆ፣ አዚፋ፣ ቡጥጫ፣ ቃርያ ስንግ፣ ብቻ ስጋን ወተትን እና የወተት ተዋጽኦን ሳይጨምር ጥሩ ጣዕም ያለዉ ለጤና በጣም ተስማሚ የሆነ ምግብ በአገራችን በጾም ወራት በተለይ በከተማዉ አካባቢ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/RA5k
ምስል picture-alliance / Bildagentur Huber

በአገራችን የሚገኙ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የፋሲካን ጾም ከጀመሩ ሶስተኛ ሳምንትን ይዘዋል። ይህ አብይ ጾም ወይም የሁዳዴ ጾም እየተባለ የሚጠራዉ የማህበር ጾም ምን ማለት ይሆን? በሁዳዴ ጾም ግዜ የሚዘጋጁ በባህላዊ ጣዕም ያላቸዉ ምግቦችስ? በአገራችን በክርስትናዉ እምነት ዘንድ የፈቃድ ጾም እና የማበር ወይም የአዋጅ ጾም መኖሩን ጽሁፎች ያሳያሉ። የፈቃድ ጾም አንድ ሰዉ በፈቃዱ የንስሃ አባቱን ጠይቆ የሚጾመዉ ሲሆን ሌላዉ በሃይማኖቱ የሚያዘዉ የማህበር ጾም መሆኑን ይሁፎች ያሳያሉ። ጥንታዊዉ እና ባህላዊዉ የኢትዮጽያ የሙዚቃ መሳርያ በገናስ ከጾሙ ጋር ምን ግንኙነት አለዉ? የለቱ ዝግጅታችን በጾሙ ትርጓሜ ጀምሮ፣ የጾም ምግብ አዘገጃጀትን አያይዞ፣ የበገና ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያችን ከጾሙ ጋር ያለዉን ግንኙነት ሊቃኝ ተዘጋጅቶአል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ