1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሄልሙት ሽሚዲት ዜና ረፍት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2008

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 30 7 2008 ዓ,ም፤ ከቀትር በኋላ በጀርመን ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩት የቀድሞዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ሄልሙት ሽሚድት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

https://p.dw.com/p/1H3ch
Verleihung des Preises der Atlantik-Brücke an Helmut Schmid
ምስል Reuters

«መንግስት ዜጎቹን በሀገር ዉስጥም ሆነ ከፊደራል ጀርመን ሪፐብሊክ ዉጭ ከስጋት በመከላከልና ደህንነታቸዉን ለመጠበቅ በሚሰጠዉ ከለላ በሕዝቡ ዘንድ ያለዉን ተዓማሚነት በማረጋገጥ የሀገራችንንም የመከላከል አቅም ማጠንከር ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ሽብርተኞችን በፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነዉ።» የቀድሞዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ሄልሙት ሽሚድት የተናገሩት ነበር።

የ 96 ዓመቱ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባል የነበሩት የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኝ ሄልሙት ሽሚዲት ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት፤ በመኖርያ ቤታቸዉ በሕክምና ሲረዱ ቆይተዉ ዛሬ ከቀትር በኋላ ሕይወታቸዉ ያለፈዉ። በአጫሽነታቸዉ የሚታወቁት የቀድሞዉ የጀርመን መራሄ መንግስት ሄልሙት ሽሚድት ወደሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ የገቡት የሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት ባበቃ በዓመቱ እንደሆነ ታሪካቸዉ ያስረዳል። ሄልሙት ሽሚድት ከመጀመርያዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ከቪሊ ብራት በመለጠቅ ከጎርጎረሳዊዉ 1974 እስከ 1982 ዓ,ም ድረስ ጀርመንን በመራሔ መንግስትነት አስተዳድረዋል።"Die Zeit" የተሰኘዉ ሳምንታዊ ጋዜጣ ተባባሪ አሳታሚ የነበሩት ሄልሙት ሽሚድ በርካታ መጻሕፍትን ለአንባብያን ያቀረቡም ነበሩ።

ሽሚት በተደጋጋሚ በጀርመናውያን ዘንድ ተወዳጁ መራሄ መንግሥታት እንደሆኑ ቢገለፅም፤ ወሳኝ እና እኔ ብቻ ትክክል ነኝ በሚል ግትር ፀባያቸውም ይታወሳሉ። ዛሬ በጀርመን ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ መሞታቸው ይፋ የሆነው የጀርመን የቀድሞ መራሄ መንግሥት ሄልሞት ሽሚት ማንነትን በተመለከተ በርሊን የሚገኘው ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን በስልክ አነጋግረነዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ