1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህንጻ ጥበበኞች

ዓርብ፣ ጥር 24 2011

አስደናቂ ህንጻዎች በጥበበኞች ይታነጻሉ። ጥበብን የያዘ የኪነ ህንጻ ባለሙያ በፈርጁ ይሰራል።

https://p.dw.com/p/3CVjF
Junge Architekten
ምስል Yamin Amin

ወጣት የሥነ ሕንፃ ባለሙያዎች

አርክቴክቸር በአማርኛው ኪነ ህንፃ የሚል ትርጓሜ አለው። ህንጻ የመገንባት ጥበብ እንደማለት ነው። 
ኪነ-ህንፃ በውበቱና በጥንካሬው ከሚመዘንባቸው ዋነኛውና መሰረታዊ መስፈርት ሆኖ በብዙዎች ዘንድ ይቀመጣል። በአለማችን እጅግ ለእይታ ውብና ሰማይ ጠቀስ የሚሏቸው ረጃጅም ህንጻዎች ተገንብተዋል። ህንፃ ተደረመሰ ብለው ከሚሰሙት ዜና በዘለለ፤  ዘመናዊነቱን የህንጻ ኪነ ጥበብም ያደንቃሉ። የህንጻ ባለሙያዎቹ ለጥንካሬው ይጨነቃል ያሉናል የዛሬ እንግዶቼ ዮሀንስ ካሳ እና ያሚን አሚን፤ በሙያቸው አርቴክቸሮች ወይም የኪነ ህንጻ ባለሙያዎች ናቸው። በ2002 ከመቀሌ ዩኒበርስቲ በአርቴክቸር እና ኤርባን ፕላንግ ተመርቀዋል። የጓደኝነት ጥምረታቸው የሚጀምረው በዩኒበርስቲ ቆይታቸው ጀምሮ ነው። የኪነ-ህንጻ ባለሙያ አብዛኛው ስራው የህንጻው ዲዛይን ላይ ያተኮረ ቢሆንም፤ የግንባታ ኢንዱስትሪውን በዋናነት ይመራል ሲል ዮሀንስ ይገልጻል። ከሀሳብ ጅማሮ የግንባታ ቦታ መረጣ እስከ ህንጻው አልቆ አገልግሎት እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ፤ የኪነ ህንጻው ባለሙያ  ስራ ነው ይለናል። ከወጣት የህንጻ ባለሙያዎቹ ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ። 

Junge Architekten
ምስል Yamin Amin