1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሀት ቃል አቀባይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 5 2013

የኦሮሞ ነጻ አውጪ ኦነግ ሸኔ በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በምህጻሩ ህወሃት ጋር ወታደራዊ ስምምነት ማድረጉን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3yrAb
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

ቃለመጠይቅ

ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው እና በትጥቅ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ኦነግ ሸኔ በመባይ የሚታወቀው ቡድን ራሱን የትግይ ኃይል ከሚለው ቡድን ጋር ወታደራዊ ስምምነት ማድረጉ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበዋል። በተመሳሳይ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ በምህጻሩ ህወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸው ኢትዮጵያን ካለችበት ቀውስ ለማውጣት ኦነግ ሸኔን ጨምሮ ከሌሎች ድርጅቶችም ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ለዶቼ ቨለ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸውን በሳተላይት ስልክ አማካኝነት ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ አግኝቼ ወቅታዊ ጉዳዮችንም አንስቼላቸዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ