1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሐት ፖለቲካ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2010

ምሁራን ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት እንደ መረብ ተሸርቧል ያሉት የድርጅቱ መዋቅር እና ህዝቡን አንቀው ይዘዋል ያሏቸው የበታች አመራሮች ሳይነኩ ከላይ የሚደረጉ ለውጦች የሚፈይዱት ነገር አይኖርም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2pErP
Äthiopien 40. Jahrestag TPLF
ምስል DW/T. Weldeyes

የህወሐት ፖለቲካ እና ትችቱ

ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) በቅርቡ ያካሄደው ግምገማ እና የወሰደው እርምጃ እንዲሁም ትናንት ያካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምደባ ነባራዊውን ሁኔታ ሊለውጥ አይችልም ሲሉ ምሁራን ተቹ። የትግራይን ክልል እና የህወሐትን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ምሁራን ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት እንደ መረብ ተሸርቧል ያሉት የድርጅቱ መዋቅር እና ህዝቡን አንቀው ይዘዋል ያሏቸው የበታች አመራሮች ሳይነኩ ከላይ የሚደረጉ ለውጦች የሚፈይዱት ነገር አይኖርም ብለዋል። ያነጋገራቸው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ ዝግዚአብሔር ዘገባ አለው።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ