1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህዳሴው ግድብ የጥናት ስምምነት

ማክሰኞ፣ መስከረም 10 2009

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ታላቅ የኤሌክትሪክ ሐይል ማመንጪያ ግድብ በከባቢ አየርና ወደ ሱዳንና ግብፅ በሚፈሰዉ የዉሐ መጠን ላይ የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ የተመረጡት ኩባንያዎች ዛሬ የሥራ ኮንትራቱን በይፋ ተፈራረሙ።

https://p.dw.com/p/1K5bP
Äthiopien Grand Renaissance Staudamm
ምስል Reuters/T. Negeri

[No title]



የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ ባለሥልጣናት በተስማሙት መሠረት BRL እና አርቴሊያ የተባሉ ሁለት የፈረንሳይ ኩባንዮች ጥናቱን እንዲያደርጉ ባለፈዉ ዓመት መጀመሪያ ላይ ተመርጠዉ ነበር።የሁለቱ ኩባንያዎች ተጠሪዎች ዛሬ ካርቱም-ሱዳን ዉስጥ ስምምነቱን በይፋ የተፈራረሙት የሰወስቱ ሐገራት የዉሐ ሚንስትሮች በተገኙበት ነዉ።የኢትዮጵያ የዉሐ፤የመስኖ እና የኤሌክትሪክ ሚንስቴር ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ አስቴር ተክሌ እንዳስታወቁት የዛሬዉ ስምምነት በሰወስቱ ሐገራት መካከል የነበረዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚረዳ ነዉ።የBRL የበላይ ሐላፊ ጊለስ ሮኩሊያን እንዳሉት ደግሞ ጥናቱ ከሁለት ወር በኋላ ተጀምሮ በአስራ-አንድ ወራት ይጠናቀቃል።ኢትዮጵያ ከአራት ዓመት በፊት በአባይ ወንዝ ላይ ማስገንባት የጀመረችዉ ግድብ በመጪዉ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።የሕዳሴ ወይም ታላቁ ተብሎ የሚጠራዉ ግድብ ወደ ግብፅ የሚፈሰዉን የዉሐ መጠን ይቀንሰዋል የሚለዉ ሥጋት ካይሮንና አዲስ አበባን ሲያወዛግብ ነበር። የጥናቱ ወጭ በጋራ የሚሸፈን ሲሆን መረጃ በተገቢዉ መንገድ ባለመስጠት ሂደቱን ያዘገዬ ሃገር ለዚህ የሚወጣዉን ተጨማሪ ወጭ የሚሸፍን ይሆናል።


ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ