ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ አሻቀበ 24.04.2024
በአማራና ትግራይ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ያለፈው ሰኞ አስታውቋል። እንደ ድርጅቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ በተለይ ሴቶችና ህጻናት የሚገኙበት ሁኔታም አሳሳቢ ነው።