የሉሲ አሟሟት ዉዝግብ

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:45 ደቂቃ
07.09.2016

የሉሲ አሟሟት ዉዝግብ

አጥኚዎቹ ለዚሕ መላምታቸዉ ማረጋገጪያ ያደረጉት በአፅሙ ላይ የደረሰ ስብራትና መጋጋጥን ነዉ።ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን የነዶክተር ካፕልማንን መላምት አይቀበሉትም።

እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ1974 አዋሽ ሸለቆ-ሐዳር ዉስጥ ቅሬተ-ዓፅሟ የተገኘዉ ሉሲ ወይም ድንቅነሽ የሞተችበት ምክንያት እንደ አፅሟ አስደናቂነት ሁሉ የአስደናቂ ክርክር ሰበብ ሆኗል።በአፅሙ ላይ ጥናት ያደረጉት ዶክተር ጆን ካፕልማንና ባልደረቦቻቸዉ እንደሚሉት ሉሲ የሞተችዉ ከዛፍ ቅርጭፍ ላይ ወድቃ በደረሰባት አደጋ ሳይሆን አይቀርም።አጥኚዎቹ ለዚሕ መላምታቸዉ ማረጋገጪያ ያደረጉት በአፅሙ ላይ የደረሰ ስብራትና መጋጋጥን ነዉ።ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን የነዶክተር ካፕልማንን መላምት አይቀበሉትም።በአፅሙ ላይ የሚታየዉ ስብራትም ሉሲ ከሞተች በኋላ በነበረዉ ረጅም ዘመን በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም ሌላ የተፈጥሮ መቀያየር ምክንያት የተከሰተ ነዉ ባይ ናቸዉ።

ሊንዳ ሽታዉደ/ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተዛማጅ ዘገባዎች

ተከታተሉን