የሊቢያው መሪ
ረቡዕ፣ የካቲት 23 2003ማስታወቂያ
በሊቢያ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ዓመፅ ቀጥሎ ትናንት በርካታ ሰው መገደሉ ተዘገበ። ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች የውጭ መንግስታት በሊቢያ ላይ ሊሰነዘር ስለሚችል ወታደራዊ ጥቃት እየመከሩ እንደሆነም ታውቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጀቶቿንና መርከቦቿን ወደ ሊቢያ እያስጠጋች እንደሆነም ተገልጿል። በአንፃሩ የሊቢያ መንግስት ጦር ቱኒዚያን ወደሚያዋስነው የሐገሪቱ ምስራቃዊ ጠረፍ መዝመቱ ተዘግቧል። ማንተጋፍቶት ስለሺ ሂሩት መለሰ