1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ ሕዝባዊ አመፅና ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ የካቲት 18 2003

የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች የሊቢያን መንግሥት ደግፋዉ አመፀኛዉን ሕዝብ እየወጉ ነዉ የሚለዉን ዘገባ አምባሳደር ኃይሌ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።

https://p.dw.com/p/R41O
የዉጪ ዜጎች ሽሽትምስል DW

የሊቢያ ሕዝባዊ አመፅ እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ሥደተኞችን ለአደጋ አጋልጧል።መንበሩ ካርቱም የሚገኘዉ በሱዳንና በሊቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያዉያኑን ከአደጋ ለማዳንና ለመርዳት የሚያደርገዉ ጥረት በመገናኛ ችግር ምክንያት አለመሳካቱን አስታዉቋል።አምባሳደር ሐይሌ ኪሮስ እንደገለጡት ኤምባሲያቸዉ በመገናኛ ዘዴዎች ከሚሰማዉ በስተቀር ኢትዮጵያዉያኑ ሥላሉበት ሁኔታ የሚያዉቀዉ የለም።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች የሊቢያን መንግሥት ደግፋዉ አመፀኛዉን ሕዝብ እየወጉ ነዉ የሚለዉን ዘገባ አምባሳደር አይሌ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።አምባሳደሩን ነጋሽ መሐመድ በሥልክ አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ