1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት በአፍሪቃ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 23 2008

በመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች መሰረት፣ ባለፈው እሁድ ሊቢያ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ የ41 ስደተኞች አስከሬን ተገኝቶዋል።

https://p.dw.com/p/1JZ17
Bootsflüchtlinge im Mittelmeer
ምስል Getty Images/AFP/G. Bouys

[No title]

ስደተኞች ወደ አውሮጳ ለመግባት በሚያደርጉት አደገኛ የባህር ጉዞ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የቀጠለው ቀውስ ዛሬም ገና መፍትሔ እንደልተገኘለት ያሳየ መሆኑን የተመድ ልዩ የሊቢያ ልዑክ ማርቲን ኮብለር ገልጸዋል። ከህዳር ፣ 2015 ዓም ወዲህ ልዩ የሊቢያ ልዑክ የሆኑት የ63 ዓመቱ ጀርመናዊ ዲፕሎማት በሊቢያ ለሚታየው ውዝግብ ስለተጀመረው መፍትሔ ማፈላለግ ጥረት እና ስለሰሜን አፍሪቃዊቱ ሀገር ጊዚያዊ ሁኔታ ከዶይቸቬለ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ የሚቀርበው ዝግጅት ከማርቲን ኮብለር ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ መሰረት ያደረገ ነው።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
አርያም ተክሌ

እሸቴ በቀለ