1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊባኖስ ጥምር መንግስት መፍረስ

ሐሙስ፣ ጥር 5 2003

በሊባኖስ ብሄራዊው አንድነት መንግስት ትናንት ፈረሰ።

https://p.dw.com/p/Qrql
ምስል AP

ይህ የሆነው በመንግስቱ የተወከሉት አስሩ የሂዝቦላ ድርጅት እና የተጓዳኞቹ ቡድናት ሚንስትሮች በጠቅላላ እና አንድ ሌላ ሚንስትርም ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ መሆኑ ተገልጾዋል። ሚንስትሮቹ ስልጣናቸውን የለቀቁት በሰው እጅ የተገደሉት የቀድሞው የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር ራፊቅ ሀሪሪ ግድያን ያጣራው የተመድ መርማሪ ቡድን የሂዝቦላ አባላትን ሳይከስ እንደማይቀር ካስታወቀ በኋላ ነው። እአአ በ 2005 ዓም ራፊቅ ሀሪሪ በተገደሉበት የቦምብ ጥቃት ሌሎች ሀያ ሁለት ሰዎችም ህይወታቸው ጠፍቶዋል።

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ