1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊዝበኑ ውል እና የጀርመን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2001

የጀርመን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የተሻሻለው የሊዝበኑ የአውሮፓ ህብረት ውል ከጀርመን መሰረታዊ ህግ ጋር አብሮ ይሄዳል ሲል ትናንት ውሳኔ አሳልፏል ።

https://p.dw.com/p/If4y
ምስል dpa

ሆኖም ፍርድ ቤቱ ጀርመን ህጉን ከማፅደቅዋ በፊት የጀርመን የህዝብ ዕንደራሴዎችን የአውሮፓ ህግጋትን የማስፈፀም ኃይል የሚመመለከተው የሀገሪቱ ህግ እንዲጠናከር ጠይቋል ። በህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት በብሄራዊ ደረጃ የህዝብ እንደራሴዎችን ስልጣን የሚያጎለብት ህግ እሰከሚወጣ ድረስ ጀርመን የተሻሻለውን የሊዝበኑን የአውሮፓ ህብረት ውል አታፀድቅም ። ጀርመንን ጨምሮ አራት የህብረቱ አባል ሀገራት ውሉን እስካሁን አለማፅደቃቸው ተግባራዊነቱ ከታሰበው በላይ ወደኋላ ይጓትትተዋል የሚል ስጋት አሳድሯል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ፣

ተክሌ የኋላ፣